You’re invited to the 2024 Hepatitis B Foundation Gala on April 5, 2024 in Warrington, PA. Details here.

መከላከል እና ክትባት


ሄፓታይተስ ቢ እንዴት ሊይዘኝ ቻለ?

ሄፓታይተስ ቢ በደም ውስጥ በሚሰራጭ ቫይረስ አማካይነት የሚመጣ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ሄፓታይተስ ቢ ወደ ሌላ ሰው የሚተላለፍባቸው በብዛት የተለመዱ መንገዶች ቀርበዋል፦

  • በቫይረሱ ከተያዘ ደም አሊያም የሰውነት ፈሳሽ ጋር በሚደረግ የቀጥታ ግንኙነት
  • በእርግዝና ወይም በወሊድ ወቅት ከተያዘች እናት ወደ ሚወለደው ልጅዋ
  • ከተያዘ ሰው ጋር በሚደረግ ጥንቃቄ የጎደለው ወሲብ
  • መርፌዎችን በመጋራት ወይም ድጋሚ በመጠቀም (ለምሳሌ ያህል ለህገ ወጥ መድሀኒቶች መርፌ መጋራት ወይም በአግባቡ ያልተቀቀሉ መርፌዎችን ለመድሀኒት፣ ለአኩፓንቸር ለንቅሳት፣ ወይም ጆሮንና ሌላ የሰውነት ክፍልን ለመብሳት መጠቀም)
  • በአግባቡ ያልተቀቀሉ የህክምና እቃዎች ወይም መርፌዎች በመንገድ ዳር ዶክተሮች፣ የጥርስ ሀኪሞች ወይም የፀጉር አስተካካዮች ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፡፡

 

ሄፓታይተስ ቢ በድንገት ይተላለፋል እንዴ?

በጭራሽ! ሄፓታይተስ ቢ በድንገተኛ ግንኙነት አይተላለፍም፡፡ ሄፓታይተስ ቢ በአየር፣ በመተቃቀፍ፣ በመነካካት፣ በማስነጠስ፣ በማሳል፣ መፀዳጃ ቤት በመጋራትና በበሩ እጀታ አይተላለፍም፡፡ እርስዎ በሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር አብረው ቢበሉና ቢጠጡ አሊያም ቫይረሱ ያለበት ሰው ያዘጋጀውን ምግብ ቢመገቡ አይተላለፍብዎትም፡፡

በሄፓታይተስ ቢ የበለጠ ሊጠቃ የሚችለው ማነው? 

ምንም እንኳን ሁሉም በሄፓታይተስ ቢ የመያዝ የተወሰነ እድል ቢኖረውም፣ የበለጠ የመያዝ እድል ያላቸው ሰዎች ደግሞ አሉ፡፡ ስራዎ፣ የአኗኗር ዘይቤዎ ወይም ሄፓታይተስ ቢ ካለባቸው ቤተሰብ መወለድዎ በቫይረሱ የመያዝ እድልዎን ከፍ ያደርገዋል፡፡ እነዚህ በብዛት የተለመዱና "ከፍተኛ ስጋት" ያለባቸው ቡድኖች ናቸው፤ ነገር ግን እነዚህ ሁሉም አለመሆናቸው ልብ ሊባል ይገባል፡፡

  • ያገቡ ወይም ሄፓታይተስ ቢ ካለበት ሰው ጋር በቅርበት የሚኖሩ፤ ይህ አዋቂዎችን እና ህፃናትንም ይጨምራል፡፡
  • ሄፓታይተስ ቢ በብዛት ባለባቸው ሀገሮች የተወለዱ ሰዎች ወይም ሄፓታይተስ ቢ በብዛት በሚስተዋልባቸው አገሮች (ኤሽያ፣ የአፍሪካ የተወሰኑ ክፍሎች፣ ደቡብ አሜሪካ፣ ምዕራብ አውሮፓ፣ እና መካከለኛው ምስራቅ) የተወለዱ ወላጆች፡፡
  • ሄፓታይተስ ቢ በብዛት በሚታይባቸው ሀገራት (ኤሽያ፣ የአፍሪካ የተወሰኑ ክፍሎች፣ ደቡብ አሜሪካ፣ ምዕራብ አውሮፓ፣ እና መካከለኛው ምስራቅ) የሚኖሩ አሊያም ወደዛ የሄዱ ሰዎች፡፡
  • ከተለያዩ ሰዎች ጋር ወሲብ የሚፈፅሙ ጎልማሶች እና ወጣቶች
  • ከተለያዩ ወንዶች ጋር ወሲብ የሚፈፅም ወንድ
  • ከተያዘች እናት የተወለደ ህጻን
  • የጤና ባለሙያዎች እና ሌሎች ሰራተኞች ከስራቸው ጋር በተያያዘ በሚገጥማቸው የደም ንክኪ፡፡
  • ኤመርጀንሲ ፐርሶኔል
  • ከ1992 በፊት በደም ልገሳ ወቅት ወደ ተቀባዩ አሊያም አሁን ላይ ደግሞ በአግባቡ ባልታየ ደም ልገሳ ምክንያት
  • አደገኛ እፅ ተጠቃሚዎች በሚወጉት መርፌ
  • የሚነቀሱ እና ሰውነታቸውን የሚበሱ ሰዎች
  • የመንገድ ዳር ዶክተሮችን፣ የጥርስ ነቃዮችን እና ፀጉር አስተካካዮችን የሚጠቀሙ ሰዎች
  • የኩላሊት እጥበት የሚደረግለት ታማሚ
  • ተጠጋግተው ባሉ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች፣ ተቋማት ወይም በጋራ በሚጠቀሙባቸው ነገሮች፡፡

 

በሄፓታይተስ ቢ ክትባት ላይ የቀረቡ ምክረ ሐሳቦች ምንድን ናቸው?

የሄፓታይተስ ቢ ክትባት ለሁሉም ጨቅላ ህፃናትና እድሜያቸው እስከ 18 ዓመት ለሆናቸው የሚመከር መሆኑን አለም አቀፉ የጤና ድርጅትእና በአሜሪካ ያለው በሽታን የመከላከልና የመቆጣጠር ማዕከል አሳውቀዋል፡፡ በአሜሪካ ያለው በሽታን የመከላከልና የመቆጣጠር ማዕከል ከፍተኛ ስጋት ያለባቸው ቡድኖች ውስጥ ያሉ ጎልማሶች መከተብ እዳለባቸው ይመክረል፡፡

የሄፓታይተስ ቢ ክትባት አስተማማኝና ውጤታማ ሲሆን ይህም ለተወለዱ ጨቅላ ህፃናት በሙሉ እና አድሜያቸው እስከ 18 ኣመት ለሆናቸው ልጆች ይሆናል፡፡ የሄፓታይተስ ቢ ክትባት ስኳር ላለባቸው ጎልማሶች እና ከስራ ባህሪያቸው ጋር በተያያዘ፣ የአኗኗር ዘይቤያቸው፣ የኑሮ ሁኔታቸው፣ እና በተወለዱበት አገር የመያዝ እድላቸው ከፍ የሚል ከሆነ ይመከራል፡፡ ሁሉም የመያዝ ስጋት ቢኖርበትም፣ ሁሉም ጎልማሶች አደገኛ የሆነውን የጉበት በሽታ በዘላቂነት ለመከላከል የሄፓታይተስ ቢ ን ክትባት መውሰድ አለባቸው፡፡

የሄፓታይተስ ቢ ከትባት አስተማማኝ ነው?

አዎ የሄፓታይተስ ቢ ክትባት አስተማማኝ እና ውጤታማ ነው፡፡  ይህ የመጀመሪያው “የፀረ ካንሰር ክትባት”ነው፤ ምክንያቱም በአለም ላይ ለጉበት ካንሰር መከሰት 80% ምክንያት የሆነውን ከሄፓታይተስ ቢ ይከላከላል፡፡ 

በአለም ላይ ከተሰጡት ከአንድ ቢሊየን በላይ መርፌዎች ላይ በተደረገ የህክምና ሳይንሳዊ ምርመራ ያመላከተው የሄፓታይተስ ቢ ክትባት አንዱና በጣም አስተማማኝ መሆኑን ነው፡፡


ክትባቱን በመከተብ ሄፓታይተስ ቢ ሊይዘኝ ይችላል?

በጭራሽ፣ ክትባቱን በመውሰድ ሄፓታይተስ ቢ አትያዝም፡፡ ክትባቱ የተሰራው በቤተ ሙከራ ውስጥ ከሴንቴቲክ ይስት ምርት ነው፡፡ በብዛት የሚስተዋለው የጎንዮሽ ጉዳት መርፌው በተወጋበት ክንድ ላይ የመቅላት እና የህመም ስሜት መኖሩ ነው፡፡

የሄፓታይተስ ቢ ክትባት መርሀግብር ምንድን ነው?

የሄፓታይተስ ቢ ክትባት በዶክተርዎ ቢሮ ውስጥ እንዲሁም በአቅራቢዎ ባለ የጤና ተቋም ወይም ክሊኒክ ውስጥ ይገኛል፡፡ የሄፓታይተስ ክትባቶችን ወስዶ ለመጨረስ ሶስት ክትባቶችን መውሰድ አስፈላጊ ሲሆን፤ እድሜያቸው ከ11 እስከ 15 ዓመት ለሆናቸው በተከታታይ የሚሰጡ ሁለት ክትባቶች ያሉ ሲሆን በአሜሪካ የምግብ እና የመድሀኒት አስተዳደር 2 ዓይነት ክትባቶች ለጎልማሶች መሰጠት እንዳለበት በ2017 አረጋግጧል፡፡ ማስታወስ ያለብን ነገር በቫይረሱ ከተያዘች እናት የተወለደ ህፃን በመጀመሪያዎቹ 12 ሰዓታት ውስጥ የመጀመሪያውን ክትባት ማግኘት አለበት፡፡

  • 1ኛው ክትባት- የተወለደው ህፃን በተወለደበት ክፍል እንዳለ ሊሰጠው ይገባል
  • 2ኛው ክትባት- 1ኛው ክትባት ከተሰጠው ከአንድ ወር (28 ቀናት) በኋላ
  • 3ኛው ክትባት- ከስድስት ወራት በኋላ የመጀመሪያው ክትባት ከተሰጠው (ወይም ቢያንስ ከ2 ወራት በኋላ 2ኛው ክትባት ከተሰጠው)

የግዴታ 16 ሳምንታት መኖር የግድ ነው፣ በ1ኛውእና በ3ኛውክትባት፡፡ የክትባት መርሀ ግብሩ ከተቋረጠ፣ ከታዘዘው በላይ መውሰድ ተገቢ አይደለም፡፡ ካቆሙበት መጀመር ይቻላል፤ ምንም እንኳን በርካታ ዓመታት ቢቆጠሩም፡፡

ከሄፓታይተስ ቢ ራስዎን የጠበቁ ስለመሆንዎ እርግጠኛ ለመሆን ቀላል የደም ምርመራ በማድረግ “የሄፓታይተስ ቢ አንቲቦዲ ምርመራ” (HBsAb) ክትባቱ ስኬታማ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማግኘት ይቻላል፡፡


ከሄፓታይተስ ቢ ራሴን ለመጠበቅ ሌላ ማድረግ ያለብኝ ነገር ምንድን ነው?

ሄፓታይተስ ቢ የሚተላለፈው በተበከለ ደምና በተበከለ የሰውነት ፈሳሽ ስለሆነ፤ ክትባቱ እስከሚያልቅ ድረስ ሊከሰቱ ከሚችሉ መያዞች ራስዎን ለመጠበቅ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ቀላል ተግባራት አሉ፡፡

  • በቀጥታ ደምንም ሆነ የሰውነት ፈሳሽን ከመንካት መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡
  • ከወሲብ አጋርዎ ጋር ኮንዶም ይጠቀሙ
  • ህገ ወጥ የሆኑ መድሀኒቶችን እና የተሳሳተ የመድሀኒት ትዕዛዝን ከመጠቀም እንዲሀም ከመወጋት መቆጠብ ያስፈልጋል
  • ስለታም የሆኑ ነገሮችን ለምሳሌ እንደ ምላጭ፣ የጥርስ ቡርሽ፣ የጆሮ ኩክ ማፅጃ፣ እና የጥፍር መቁረጫ በጋራ መጠቀምን ማስወገድ ያስፈልጋል
  • ለህክምና፣ ለጥርስ ህክምና፣ ለደረቅ መር ህክምና፣ ለንቅሳት፣ እንዲሁም ጆሮን እና ሌላውን የሰውነት ክፍል ለመብሳት የተቀቀሉ መርፌዎችንና ሌሎች መገልገያዎችን መጠቀማችንን እርግጠኛ መሆን አለብን
  • የፈሰሰ ደምን ለማፅዳት ጓንት ማድረግ እንዲሁም ያልቆየና ንፁህ ውሀ መጠቀም ያስፈልጋል
  • ደም ከነኩ ወይም ካፀዱ በኋላ እጅን በውሀና በሳሙና በሚገባ መታጠብ ያስፈልጋል
  • ከምንም በላይ የሄፓታይተስ ቢ ን ክትባት መውሰድዎን እርግጠኛ ይሁኑ!

 

 

Prevention and Vaccination 

How can I get hepatitis B?
Hepatitis B is an infectious disease caused by a virus that is spread through blood. Listed below are the most common ways hepatitis B is passed to others:

  • Direct contact with infected blood or infected bodily fluids 
  • From an infected mother to her newborn baby during pregnancy or delivery 
  • Unprotected sex with an infected partner 
  • Shared or re-used needles (for example, sharing needles for illegal drugs or re-using needles that are not properly sterilized for medicine, acupuncture, tattoos, or ear/body piercing) 
  • Unsterilized medical equipment or needles that may be used by roadside doctors, dentists or barbers

 

Is hepatitis B transmitted casually?
No, hepatitis B is not spread through casual contact. You cannot get hepatitis B from the air, hugging, touching, sneezing, coughing, toilet seats or doorknobs. You cannot get hepatitis B from eating or drinking with someone who is infected or from eating food prepared by someone who has hepatitis B.

Who is most likely to become infected with hepatitis B? 
Although everyone is at some risk for getting hepatitis B, there are some people who are more likely to get infected. Your job, lifestyle, or just being born into a family with hepatitis B can increase your chances of being infected. Here are some of the most common "high risk" groups -- but please remember that this is not a complete list:

  • People who are married to or live in close household contact with someone who has hepatitis B. This includes adults and children.
  • People who were born countries where hepatitis B is common, or whose parents were born in countries where hepatitis B is common (Asia, parts of Africa and South America, Eastern Europe, and the Middle East). 
  • People who live in or travel to countries where hepatitis B is very common (Asia, parts of Africa and South America, Eastern Europe, and the Middle East).
  • Sexually active adults and teenagers 
  • Men who have sex with men 
  • Infants born to infected mothers 
  • Healthcare workers and others who are exposed to blood in their jobs.
  • Emergency personnel 
  • Patients who are on kidney dialysis
  • Residents and staff of group homes, institutions, or correctional facilities.
  • Recipients of blood transfusions before 1992, or more recent recipients of improperly screened blood
  • Injection drug users, past and present 
  • People who get tattoos or body piercing 
  • People who use roadside doctors, dentists or barbers

 

What are the recommendations for the hepatitis B vaccine?

The hepatitis B vaccine is recommended for all infants and children up to age 18 years by the World Health Organization (WHO) and the U.S. Centers for Disease Control and Prevention (CDC). The CDC also recommends that adults in high-risk groups be vaccinated.

The hepatitis B vaccine is a safe and effective vaccine that is recommended for all infants at birth and for children up to 18 years. The hepatitis B vaccine is also recommended for adults living with diabetes and those at high risk for infection due to their jobs, lifestyle, living situations, or country of birth. Since everyone is at some risk, all adults should seriously consider getting the hepatitis B vaccine for a lifetime protection against a preventable chronic liver disease.

 

Is the hepatitis B vaccine safe? 
Yes, the hepatitis B vaccine is very safe and effective. In fact, it is the first “anti-cancer vaccine” because it can protect you from hepatitis B, which is the cause of 80% of all liver cancer in the world.

With more than one billion doses given throughout the world, medical and scientific studies have shown the hepatitis B vaccine to be one of the safest vaccines ever made.

 

What is the hepatitis B vaccine schedule?
The hepatitis B vaccine is available at your doctor's office and local health department or clinic. Three doses are generally required to complete the hepatitis B vaccine series, although there is an accelerated two-dose series for adolescents age 11 through 15 years, and there is a new 2-dose vaccine that was approved by the U.S. Food and Drug Administration (FDA) for use in adults in 2017. It is important to remember that babies born to infected mothers must receive the first dose of hepatitis B vaccine in the delivery room or within the first 12 hours of life.

1st Shot - At any given time, but newborns should receive this dose in the delivery room
2nd Shot - At least one month (or 28 days) after the 1st shot
3rd Shot - Six months after the 1st shot (or at least 2 months after the 2nd shot)

There must be at least 16 weeks between the 1st and 3rd shot. If your vaccine schedule has been delayed, you do not need to start the series over, you can continue from where you have left off – even if there have been years between doses.

To be certain that you are protected against hepatitis B, ask for a simple blood test to check your “hepatitis B antibody titers” (HBsAb) which will confirm whether the vaccination was successful.

 

What else can I do to protect myself from hepatitis B?

Since hepatitis B is spread through infected blood and infected body fluids, there are several simple things that you can do to protect yourself from possible infection until your vaccination is complete:

  • Avoid touching blood or any bodily fluids directly
  • Use condoms with sexual partners
  • Avoid illegal drugs and prescription drug misuse, including injection of such drugs
  • Avoid sharing sharp objects such as razors, toothbrushes, earrings, and nail clippers
  • Make sure that sterile needles and equipment are used for medicine, the dentist, acupuncture, tattoos, ear and body piercing
  • Wear gloves and use a fresh solution of bleach and water to clean up blood spills 
  • Wash your hands thoroughly with soap and water after touching or cleaning up blood
  • Most importantly, make sure you receive the hepatitis B vaccine!