You’re invited to the 2024 Hepatitis B Foundation Gala on April 5, 2024 in Warrington, PA. Details here.

እንኳን ወደ አማርኛ የሄፓታይተስ ቢ ምዕራፍ የፋውንዴሽን ድረ ገፅ

ሄፓታይተስ ቢ ድምፅ አልባው ገዳይ ሲባል አብዛኞቹ ሰዎች እንዳለባቸው አንኳን አያውቁም፡፡ ድረ ገፁ ሄፓታይተስ ቢ ን ስለ መከላከል፣ ምርመራ ስለማድርግ፣ እና ስለመቆጣጠር መረጃ ይዟል፡፡ እርስዎ መረጃዎችን ለጓደኛዎ፣ ለቤተሰብዎ እና በአቅራቢያዎ ላሉ ማህበረሰቦች እንዲያጋሩ እንጠይቆታለን፡፡ ስለ ሄፓታይተስ ቢ ሊያስታውሷቸው የሚገቡ ጠቃሚ የሆኑ ነገሮች እነሆ፦

  • ሄፓታይተስ ቢ በመወለድ አይተላለፍም- በቫይረስ ነው የሚመጣው፡፡ 
  • እድሜ ልክህን ከሄፓታይተስ ቢ የሚጠብቅህ አስተማማኝ ክትባት አለ፡፡ 
  • ሄፓታይተስ ቢ እንዳለ ለማወቅ ቀላል የደም ምርመራ አለ፡፡
  • የመከላከያ ህክምናዎች አሉ፡፡

ሄፓታይተስ ቢ ዓለማቀፋዊ በሽታ ነው

ሄፓታይተስ ቢ የእድሜ እና የብሄር ልዩነት ሳያደርግ ሁሉንም ሰው ሊይዝ ይችላል፤ ነገር ግን ሄፓታይተስ ቢ በብዛት በሚከሰትባቸው ከተወሰኑ የዓለም ክፍሎች ያሉ ሰዎች ማለትም እንደ ኤሲያ፣ የአፍሪካ የተወሰኑ ክፍሎች፣ ደቡብ አሜሪካ፣ ምዕራብ አውሮፓ እና መካከለኛው ምስራቅ በበሽታው የመያዝ እድላቸው በእጅጉ ከፍ ያለ ነው፡፡ በነዚህ ቦታዎች በተወለዱ አሜሪካውያን (ወይም ቤተሰቦቻቸው በተወለዱት) ላይ ሄፓታይተስ ቢ በብዛት ይከሰታል፡፡

በመቶ ሚሊየን በሚቆጠሩና በዓለም ዙሪያ በሚኖሩ ሰዎች ሄፓታይተስ ቢ አለባቸው፡፡ በርካታ ሰዎች በበሽታው ስለመያዛቸው እንኳን አያውቁም፤ እንዲሁም የበሽታው ምልክቶችም አይታይባቸውም፤ ነገር ግን ማወቅ ያለባችሁ በርካታ ጠቃሚ ነገሮች አሉ፡፡ ሄፓታይተስ ቢ በደም ውስጥ እንዳለና እንደሌለ ማረጋገጥ ህይወትዎን ያድናል፡፡ ሄፓታይተስ ቢ እንዳለብዎ ካወቁ፣ የአኗኗር ዘይቤዎትን በመለወጥ የጉበትዎን ጤንነት ከመጠበቅ ባለፈ ዶክተሮች ቫይረሱን እንዲቆጣጠሩት እና ጉበትዎም እንዳይጎዳ ያደርጋሉ፡፡

የሄፓታይተስ ቢ ፋውንዴሽን ለትርፍ ያልተቋቋመ ብሄራዊ ድርጅት ሲሆን ጥናትና ምርምር፣ ትምህርት እና ታማሚዎችን ማማከር ስራዎች ላይ በማተኮር፣ በሽታውን ለማከም ብሎም በመላው ዓለም ያሉና በሄፓታይተስ ቢ የተያዙ ሰዎች በሙሉ ህይወታቸው እንዲሻሻል የሚሰራ ነው፡፡

መግለጫ፦ በድረ ገፅ የተለቀቁት መረጃዎች ለትምህርት አገልግሎት ብቻ የሚውሉ ናቸው፡፡ የሄፓታይተስ ቢ ፋውንዴሽን የህክምና ተቋም አይደለም፡፡ በግልዎ ጤናዎትን ለመጠበቅ እና ምክር ለማግኘት ዶክተር አሊያም ብቁ የጤና ባለሙያ ማነጋገር አለብዎት፡፡

Welcome to the Amharic Chapter of the Hepatitis B Foundation Website

Hepatitis B is known as a silent disease, and most people don’t even know they are infected. This website contains information about preventing, diagnosing and managing hepatitis B. We encourage you to share this information with your friends, family and others in your community. Here are some important things to remember about hepatitis B:

  • Hepatitis B is not inherited - it is caused by a virus. 
  • There is a safe vaccine which will protect you from hepatitis B for life. 
  • There is a simple blood test to diagnose hepatitis B. 
  • There are treatment options.

Hepatitis B is a Global Disease
Hepatitis B can infect any person of any age or ethnicity, but people from parts of the world where hepatitis B is common, such as Asia, parts of Africa and South America, Eastern Europe, and the Middle East, are at much higher risk for getting infected. Hepatitis B is also common among Americans who were born (or whose parents were born) in these regions.

There are hundreds of millions of people worldwide who have hepatitis B. Most people don’t even know they are infected, and don’t have symptoms – but there are many important things you should know. Getting tested for hepatitis B can save your life. If you know you have hepatitis B, you can make lifestyle choices to keep your liver healthy and you can see a doctor to help manage the virus and prevent liver damage.

The Hepatitis B Foundation is a national nonprofit organization dedicated to finding a cure and helping to improve the quality of life for all those affected by hepatitis B worldwide through research, education and patient advocacy.

Disclaimer: The information that is provided on this website is for educational purposes only. The Hepatitis B Foundation is not a medical organization. Please talk to your doctor or a qualified health care provider for personal medical care and advice.